Vancouver, BC info@ecasocial.com 604.123.4567

Funerals የቀብር ሥነ ስርዓት

የሟች ቤተሰብ / ዘመድ አዝማድ / በቅርብ ከሌለ ዘመድ አዝማዱ  ኢትዮጵያዊያኖች መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሙሉ ሐላፊነቱን  ኮሚቴው በመውሰድ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል
  • በተቻለ መጠን የሟችን ቤተሰብ ወይም የቅርብ ዘመድ በማፈላለግ መርዶውን ማርዳትና ሊደረግ የሚገባውን ነገር በሙሉ መወያየት ፣ ለችግሮች ሙሉ መፍትሄ እስኪገኝ   የቅርብ ግንኙነትን  ማጠናከር ፤
  • የሟችን የቀብር ሥነ ሥርዓት  ለማስፈፀም ከሚመለከታቸው  የመንግሥት ፣ የግል….ወዘት ድርጅቶች ጋር ግንኙነት መፍጠር ፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ  ከማህበረሰቡ ዕርዳታ በማሰባሰብ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ማስፈፀም ፤
  • የሟች ሕጋዊ ወራሾች በቦታው እስኪገኙ ወይም ሕጋዊ ውክልና ያለው እስኪቀርብ ድረስ የሟች ንብረት እንዳይባክን ከሚመለከተው የመንግሥት ሆነ የግል ድርጅት ጋር ተባብሮ በመስራት ንብረቶቹ ተጠብቀው እንዲቆዩ አስፈላጊውን ጥንቃቄና ጥረት ማድረግ ፤
  • የሟች ቤተሰብ በርቀት ምክንያት የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ለማስፈፀምና ለመከታተል ሳይቻለው ቢቀርና ሥነ ሥርዓቱ በፎቶግራፍና በፊልም እንዲቀረፅላቸውና እንዲላክላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡ ፤ ውይም ኮሚቴው የቅርብ ቤተሰቦችን ማግኘት ሳይችል የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ካከናወነ በኁላ ወደፊት ለሚያገኛቸው ቤተሰቦች ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን በፎቶግራፍና በፊልም  አስቀርፆ ይልካል ፣ያስቀምጣል ፤
  • በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ኮሚቴው የሟቹን የሕይወት ታሪክ አጠር ባለ መልኩ በማዘጋጀት፣ ከኮሚቴው አባል ወይም ከኮምዩኒቲው የስራ አመራር በአንዱ ለሕዝቡ ያስደምጣል፤
ሟች ቤተሰብ ወይም የቅርብ ዘመድ በአጠገቡ ካሉት ።
  • የሟች ቤተሰብ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ለማስፈጸም የሚያወጣውን መመሪያ በመከተልና በማክበር ኮሚቴው ከሟች ቤተሰብ ጎን በመቆም አቅም በፈቀደው መሰረት እርዳታ መለገሥና የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ማስፈጸም ፤
  • የቀብር ሥነ ሥርዓቱ የሚፈጸምበትን ሰዓት ፣ ቀንና ቦታ ከሟች ምስል ጋር በማጣመር ፤ አመቺ የሆነ መገናኛ ዘዴ በመጠቀም እና በማሕበሩ ድረ ገጽ ላይ በማውጣት ሕብረተሰቡ የሃዘን ተካፋይ እንዲሆን መቀስቀስና ማሳወቅ ፤
ኮሚቴው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የማኅበራችን አባል የሆነ ወይም ያልሆነ ከዚህ አለም በሞት በሚለዩበት ጊዜ፣ በቀብር ስነ ሥርዓቱ ላይ ለሁሉም ተመሳሳይ ወጪ በማድረግ የአበባ ጉንጉን በኢትዮጵያ ማኅበር ስም አዘጋጅቶ በቀብር ስነ ሥርዓቱ ላይ ያኖራል።
ማንኛውም ሰው ራሱን ሲያጠፋ፣ በሰው እጅ ሲገደል ወይም በተለያዪ አደጋዎች ሲሞት፤ የሞተበትን ምክንያት ለማጣራት ሲባል ጉዳዪ   በፖሊስ እጅ  ስለሚገባ  የቀብር  ሥነ ሥርአቱን  በወቅቱ  ለማካሄድ በፈጽሞ አስቸጋሪ ከመሆኑ ባሻገር ያለ ፖሊስ ፈቃድ አስከሬኑን ከሆስፒታል ማግኘት በፈጽሞ የማይቻል  ነው፤   በባህላችን አስከሬን ውሎ ማደር የሌለበት እንደመሆኑ መጠን ኮሚቴው ከሆስፒታል እና ከፖሊስ ጋር ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ አስከሬኑ ከፖሊስ እጅ ወቶ በጊዜው የቀብሩ ሥነ ሥርዐት የሚፈጸምበትን ሁኔታ ማመቻቸት።

 

He / she shall take the following duties and responsibilities of the deceased Family / relative to the full extent of his / her family relationship:

Talk to the family of the deceased or a close relative, discuss the things that should be done, and strengthen the close relationship until the solution is complete.

Establishing relationships with the government, private individuals, etc. in order to perform the funeral of the deceased person and undertake the funeral service where necessary as necessary from the community.

Take necessary precautions and efforts to ensure that the assets are preserved by cooperating with the public and private enterprise concerned to ensure that the deceased helically may be present or legally represented

If the family of the deceased is not able to carry out the funeral for the funeral of the deceased and request that the ceremony be shaped and sent for photographic and film festivals or the funeral service may notify the families of future families, the committee may record and keep the funeral service in photographic and film photography.

At the funeral service, the committee shall prepare briefly the biographical bias of the deceased and conduct one of the members of the committee or the management of the community; If the deceased family or immediate relative is next to him.

Following and following the instructions provided by the family of the deceased, the committee should stand side by side with the family of the deceased, and give support and funeral service to the funeral, Encourage the time, date, and place of the funeral process with the deceased person, use the appropriate media and participate in mourning participation on the community web site;

When the committee commemorates the death of any Ethiopian or ancestor member of this association, he will make the funeral service on the funeral service, with the same amount of funeral expenses on the funeral ceremony.

When a person commits suicide, he is killed by the hands, or he dies in certain dangers, the police are involved in investigating the cause of the death, and it is impossible for the police to obtain the body of the deceased from the hospital. By striving to keep up with the police, it is necessary to facilitate the eventual secession of the corpses from the police.